ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣
ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ ፍየሎች፣ ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የዔናን ልጅ አኪሬ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።