ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣
ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው ተባዕት የበግ ጠቦት፣
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።