እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።
ከዮሴፍ ልጆች ከኤፍሬም የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ፤ ከምናሴ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል፤
በምዕራብ በኩል፤ የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣
ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣
በስምንተኛው ቀን የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ስጦታውን አመጣ፤