ለኀጢአት መሥዋዕት አንድ ተባዕት የፍየል ጠቦት፣
ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ አንድ ወይፈን፣ አንድ አውራ በግ፣ አንድ ዓመት የሆነው የበግ ጠቦት፣
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።