እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፤
አሮንም እጆቹን ወደ ሕዝቡ ዘርግቶ ባረካቸው፤ የኀጢአት መሥዋዕቱን፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የኅብረቱን መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ ወረደ።
“ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ለእግዚአብሔር ለሚሳል ናዝራዊ ሕጉ ይኸው ነው፤ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ለሚገባው ነገር እንደ ናዝራዊነቱ በተሳለው መሠረት መሆን አለበት። በናዝራዊነት ሕግ መሠረት የተሳለውን ስእለት መፈጸም ይገባዋል።’ ”
“አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሏቸው፤
እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፣ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጕዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፣ አምላክህ እግዚአብሔር መርጧቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።