በመሶብ ያለውን ቂጣ፣ እንዲሁም አውራ በጉን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ከእህሉና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ ካህኑ ለእግዚአብሔር ያቅርብ።
በሌማት ላይ አድርገህ ከወይፈኑና ከሁለቱ አውራ በጎች ጋራ አቅርባቸው።
“ ‘ካህኑ እነዚህን የኀጢአት መሥዋዕትና የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርባል።
“ ‘ከዚያም ናዝራዊው ተስሎ የተለየበትን ጠጕር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጨው፤ ጠጕሩንም ወስዶ ከኅብረቱ መሥዋዕት ሥር በሚነድደው እሳት ውስጥ ይጨምረው።