እስራኤላውያን ይህንኑ አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈር አስወጧቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ፈጸሙ።
ንጉሥ ዖዝያን እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጽ ነበረበት። ለምጻም በመሆኑም ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተወግዶ ነበርና በተለየ ቤት ተቀመጠ። በዚያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን በኀላፊነት የሚመራውና የአገሩንም ሕዝብ የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር።
እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።
እስራኤላውያን በሙሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ያዘዘውን ሁሉ ፈጸሙ።
ወንድም ሆነ ሴት አስወጡ፤ እኔ በመካከላቸው የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈር አስወጧቸው።”
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤