ወይም አንድ ሰው ሚስቱን ከመጠርጠሩ የተነሣ የቅናት መንፈስ ሲያድርበት በእግዚአብሔር ፊት ያቁማት፤ ካህኑም ሕጉ በሙሉ በሴቲቱ ላይ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ያድርግ።
ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና በርግጥም ጐድፋ ብትገኝ ወይም ባሏ የቅናት መንፈስ ዐድሮበት ቢጠረጥርና እርሷ ግን ጐድፋ ባትገኝ፣
“ ‘እንግዲህ የቅናት ሕግ ይህ ነው፤ አንዲት ሴት በትዳር ላይ እያለች ወደ ሌላ ሄዳ ከረከሰች፣
ባልየውም ከበደል ንጹሕ ይሆናል፤ ሴትዮዋ ግን በበደሏ ምክንያት የሚመጣውን ፍዳ ትቀበላለች።’ ”