በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ዐምሳ ነበሩ።
ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት ሆኗቸው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል የመጡት ወንዶች ሁሉ፣
ይህ ከቀዓት ጐሣዎች ሁሉ በመገናኛው ድንኳን ያገለገሉት ሰዎች ጠቅላላ ድምር ነው። ሙሴና አሮን፣ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት እነዚህን ቈጠሯቸው።