Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘኍል 4:15

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና ዕቃዎቹን፣ ንዋየ ቅድሳቱንም በሙሉ ሸፍነው ከጨረሱ በኋላ ሰፈሩ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሲሆን፣ ቀዓታውያን ለመሸከም ይምጡ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን መንካት የለባቸውም፤ ስለዚህ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያሉትን እነዚህን ዕቃዎች የሚሸከሙ ቀዓታውያን ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሳዶቅም በዚያ ነበር፤ ዐብረውት የነበሩትም ሌዋውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት ተሸክመው ነበር። እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ዐሳረፉ፤ አብያታርም ሕዝቡ በሙሉ ከከተማዪቱ ለቅቆ እስኪወጣ ድረስ መሥዋዕት አቀረበ።

እነዚያ የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት ርምጃ በሄዱ ቍጥር፣ አንድ በሬና አንድ የሠባ ጥጃ ይሠዋ ነበር።

የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በመጡ ጊዜ፣ ካህናቱ ታቦቱን አነሡ፤

ሙሴ በእግዚአብሔር ቃል እንዳዘዘው፣ ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦት በትከሻቸው ላይ በመሎጊያዎች አድርገው ተሸከሙ።

ከዚያም ዳዊት፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከም” ሲል አዘዘ።

ሌዋውያን ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኑን ወይም የመገልገያ ዕቃውን ሁሉ መሸከም የለባቸውም።”

በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አበጅተህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም ግርጌውን እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ማንም ተራራውን ቢነካ በርግጥ ይሞታል።

እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለማየት በመጣደፍ ብዙዎቹ እንዳይጠፉ ውረድና አስጠንቅቃቸው

በሸክም ጊዜ በመሠዊያው ሁለቱም ጐኖች እንዲሆኑ፣ መሎጊያዎቹ በቀለበቶቹ ውስጥ ይግቡ።

እንዳይሞትም የዕጣኑ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለውን ስርየት መክደኛ ይሸፍነው ዘንድ፣ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምረው።

በዚህ ፈንታ ሌዋውያንን በምስክሩ ማደሪያ፣ በውስጡ ባሉት በመገልገያ ዕቃዎች ሁሉ እንዲሁም ከዚሁ ጋራ በተያያዙ በማናቸውም ነገሮች ላይ ኀላፊዎች ይሁኑ፤ ማደሪያውንና በውስጡ ያሉትን የመገልገያ ዕቃዎች ይሸከሙ፤ በውስጡ ያገልግሉ፤ ድንኳናቸውንም በዙሪያው ይትከሉ።

ማደሪያው በሚነሣበት ጊዜ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያው በሚተከልበትም ጊዜ ሌዋውያን ያቁሙት፤ ሌላ ሰው ቢቀርብ ግን ይገደል።

ከዚህ በኋላ ቀዓታውያን ንዋያተ ቅድሳቱን ተሸክመው ተጓዙ፤ እነርሱ ከመድረሳቸው በፊት ማደሪያው ተተክሎ ነበር።

እነርሱም በአንተ ኀላፊነት ሥር ሆነው የድንኳኑን አገልግሎት በሙሉ ያከናውኑ፤ ይሁን እንጂ ወደ መቅደሱ ዕቃዎችም ሆነ ወደ መሠዊያው አይጠጉ፤ ከተጠጉ ግን እነርሱም አንተም ትሞታላችሁ።

ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ ከማደሪያው ድንኳን በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ ከመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይሰፍራሉ። እነርሱም እስራኤላውያንን ወክለው ማደሪያ ድንኳኑን ለመጠበቅ ኀላፊዎች ይሆናሉ። ወደ ማደሪያው ድንኳን የሚቀርብ ማንኛውም ሌላ ሰው ግን ይገደል።

ከዚያም ለመሠዊያው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች በሙሉ፣ የእሳት ማንደጃዎቹን፣ ሜንጦዎቹን፣ የእሳት መጫሪያዎቹንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን በላዩ ላይ ያድርጉ፤ በእነዚህም ላይ የአቆስጣ ቍርበት መሸፈኛ አልብሰው መሎጊያዎቹን በየቦታቸው ያስገቡ።

ወደ ንዋየ ቅድሳቱ በሚቀርቡበትም ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ አንተ ይህን አድርግላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ይግቡ፤ እያንዳንዱንም ሰው በየሥራው ላይ ይደልድሉት፤ ምን መሸከም እንዳለበትም ያስታውቁት።

ቀዓታውያን ግን ንዋየ ቅድሳቱን ለአንድ አፍታ እንኳ ለማየት አይግቡ፤ ቢገቡ ይሞታሉ።”

በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው መሸከም ስለ ነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም።

ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ፣ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ ለሌዊ ልጆች፣ ለካህናቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ።

ሙሴ ለኢያሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲነግር ኢያሱን ያዘዘው እስኪፈጸም ድረስ፣ ታቦቱን የተሸከሙት ካህናት በዮርዳኖስ መካከል ቆመው ቈዩ፤ ሕዝቡም ፈጥነው ተሻገሩ፤

ነገር ግን እግዚአብሔር ከቤትሳሚስ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ወደ እግዚአብሔር ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ እግዚአብሔር እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሰ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች