እያንዳንዱ እስራኤላዊ የየአባቶቹን ርስት መውረስ ስላለበት፣ በማንኛውም የእስራኤል ነገድ ውስጥ ርስት የምትወርስ የትኛዪቱም ሴት፣ ከአባቷ ነገድ ወገን የሆነውን አንዱን ማግባት አለባት።
አልዓዛር ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱንም የአጎታቸው የቂስ ልጆች አገቧቸው።
እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የወረሰውን መሬት እንዳለ ማቈየት ስላለበት፣ ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍም።”