ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ።
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤
“እስራኤላውያን ተመልሰው በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት አጠገብ እንዲሰፍሩ ንገራቸው፤ በበኣልዛፎንም አንጻር በባሕሩ አጠገብ ይስፈሩ።
ግብጻውያን፣ ይኸውም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገላዎች፣ ፈረሰኞችና እግረኞች ሁሉ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው፤ በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ በፊሀሒሮት ሰፍረው ሳሉ ደረሱባቸው።
ከፊሃሒሮት ተነሥተው በባሕሩ ውስጥ በማለፍ ወደ ምድረ በዳው ሄዱ፤ ከዚያም በኤታም ምድረ በዳ ሦስት ቀን ተጕዘው በማራ ሰፈሩ።