ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።
ይህም ከመጠጥ ቍርባኑ ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ በየሰንበቱ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።
ከወይፈኑ፣ ከአውራ በጉና ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
“ ‘ከስእለትና ከበጎ ፈቃድ ስጦታዎቻችሁ በተጨማሪ፣ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁን፣ የእህል ቍርባኖቻችሁን፣ የመጠጥ ቍርባኖቻችሁንና የኅብረት መሥዋዕቶቻችሁን በበዓላታችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።’ ”