ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት አቅርቡ።
“ ‘በስድስተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ስምንት ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።
ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።