Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘኍል 29:22

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ፣ ሐዘናቸው ይበዛል፤ እኔ ግን የደም ቍርባናቸውን አላፈስስም፤ ስማቸውንም በአፌ አልጠራም።

ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።

የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን፣ ከእግዚአብሔር ቤት ተቋርጧል፤ በእግዚአብሔርም ፊት የሚያገለግሉ፣ ካህናት ያለቅሳሉ።

በምሕረቱ ተመልሶ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የሚሆነውን፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን እንዲተርፋችሁ፣ በረከቱን ይሰጣችሁ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?

ከወይፈኖቹ፣ ከአውራ በጎቹና ከበግ ጠቦቶቹ ጋራ የእህል ቍርባናቸውንና የመጠጥ ቍርባናቸውን በተወሰነው ቍጥር መሠረት ዐብራችሁ አቅርቡ።

“ ‘በአራተኛው ቀን ሁሉም እንከን የሌለባቸው ዐሥር ወይፈኖች፣ ሁለት አውራ በጎችና ዓመት የሆናቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች አቅርቡ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች