ከሰባቱም የበግ ጠቦቶች ከእያንዳንዳቸው ጋራ የኢፉ አንድ ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቅረብ።
ከእያንዳንዱም ወይፈን ጋራ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፉ ሦስት ዐሥረኛ፣ ከአውራው በግ ጋራ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት ይቀርባል፤
በተጨማሪም ማስተስረያ እንዲሆንላችሁ አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ።