የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤ በሄኖኅ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤ በፈሉስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤
ልያ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ “እግዚአብሔር መከራዬን ስለ ተመለከተልኝ፣ ከእንግዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።
እስራኤልም በዚያ ምድር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋራ ተኛ፤ እስራኤልም ድርጊቱን ሰማ። ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም፦
የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቷል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች፤ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ።
የየቤተ ሰቡ አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፣ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን፣ ከርሚ። እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው።
ከእስራኤል የበኵር ልጅ ከሮቤል ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ሆኖ በሰራዊቱ ውስጥ ለማገልገል ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
“እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።” ከግብጽ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤ በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤