የዳን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በስምዔ በኩል፣ የሰምዔያውያን ጐሣዎች። እነዚህ እንግዲህ የዳን ጐሣዎች ሲሆኑ፣
የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤
ከዳን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
እነዚህ የብንያም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ዐምስት ሺሕ ስድስት መቶ ነበሩ።
ሁሉም የሰምዔያውያን ጐሣዎች ነበሩ፤ ከእነዚህ የተቈጠሩት ደግሞ ስድሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።