እነዚህ የምናሴ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ዐምሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነበሩ።
ከጕዳትም ሁሉ የታደገኝ መልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይሥሐቅ ስም ይጠሩ፤ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።”
የኤፍሬም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሱቱላ በኩል፣ የሱቱላውያን ጐሣ፣ በቤኬር በኩል፣ የቤኬራውያን ጐሣ፣ በታሐን በኩል፣ የታሐናውያን ጐሣ፤