የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤ በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣ በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤
የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤
ከዛብሎን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።