በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤ በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤
የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤
የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤ በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤ በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤ በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤
በአሮዲ በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤ በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤