ሙሴም የእስራኤልን ዳኞች፣ “እያንዳንዳችሁ በኣል ፌጎርን በማምለክ የተባበሩትን ሰዎቻችሁን ግደሉ አላቸው።”
ከዚያም ኤልያስ፣ “የበኣልን ነቢያት ያዟቸው! አንድም ሰው እንዳያመልጥ” ሲል አዘዘ፤ ሕዝቡም ያዟቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ አውርዶ አሳረዳቸው።
ነገር ግን ችሎታ ያላቸውን ሰዎች ከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ፤ እነዚህም ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ታማኞችና በማታለል የሚገኘውን ጥቅም የሚጸየፉ ይሁኑ። የሺሕ፣ የመቶ፣ የዐምሳ፣ የዐሥር፣ አለቃ አድርገህ ሹማቸው።
“ለእግዚአብሔር በቀር ለሌላ አማልክት የሚሠዋ ይጥፋ።
ስለዚህ እስራኤል በኣል ፌጎርን በማምለክ ተባበረ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ በላዩ ነደደ።
ምናምንቴ ሰዎች ከመካከላችሁ ተነሥተው አንተ የማታውቃቸውን፣ “ሌሎች አማልክትን ሄደን እናምልክ” በማለት የከተማቸውን ሕዝብ እያሳቱ ቢሆን፣
በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሁሉ በሰይፍ ግደላቸው፤ ከተማዪቱን ከነሕዝቧና ከነቀንድ ከብቷ ፈጽሞ ደምስሳት።
የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወድዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት) “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣
ያለማመንታት ግደለው፤ እርሱንም ለመግደል በመጀመሪያ የአንተ እጅ፣ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይነሣ።
በፌጎር የተሠራው ኀጢአት አይበቃንምን? ምንም እንኳ በእግዚአብሔር ጉባኤ ላይ መቅሠፍት ቢወርድም፣ እስከ ዛሬዪቱ ዕለት ድረስ ራሳችንን ከዚያች ኀጢአት አላነጻንም።