በማግስቱም ጧት ባላቅ በለዓምን ወደ ባሞትባኣል አወጣው፤ እዚያም ሆኖ ሕዝቡን በከፊል አየ።
እርሱም ለየኰረብታው መስገጃ እንዲሁም ለሠራቸው የፍየልና የጥጃ ምስሎች የራሱን ካህናት ሾመ።
እኔም ያላዘዝኋቸውን፣ ያልተናገርኋቸውን፣ ፈጽሞም ያላሰብሁትን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን በእሳት ሊሠዉለት ለበኣል መስገጃ ኰረብቶች ሠርተዋል።
በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ ከሞዓብ አጠፋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር፤
“እሳት ከሐሴቦን ወጣ፤ ነበልባልም ከሴዎን ከተማ ተንቦገቦገ፤ የሞዓብን ዔር፣ በአርኖን ከፍታዎች የሚኖሩትንም አለቆች በላ።
ባላቅም ከብቶችና በጎች ሠዋ፤ ከፊሉንም ለበለዓምና ከርሱ ጋራ ለነበሩት አለቆች ሰጣቸው።
በለዓም፣ “እዚህ ሰባት መሠዊያ ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎችም አዘጋጅልኝ” አለው።
ከዚህ በኋላ ባላቅ፣ “እነርሱን ማየት ወደምትችልበት ወደ ሌላ ቦታ እንሂድ፤ በእዚያም ሁሉን ሳይሆን በከፊል ብቻ ታያቸዋለህ፤ እዚያም ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።
ከምድራቸው የምታስለቅቋቸው አሕዛብ በረዣዥም ተራሮች፣ በኰረብቶችና በእያንዳንዱ ዛፍ ሥር አማልክታቸውን የሚያመልኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉ።