ከዚያም በለዓም ከባላቅ ጋራ ወደ ቂርያት ሐጾት ሄደ።
ሞዓብ ወደ ኰረብታዋ ብትወጣ፣ ትርፏ ድካም ብቻ ነው፤ ለጸሎት ወደ መቅደሷ ብትገባም፣ ዋጋ የለውም።
በለዓምም፣ “ይኸው አሁን መጥቻለሁ፤ ግን እንዲያው ማንኛውንም ነገር መናገር እችላለሁን? እኔ መናገር የሚገባኝ እግዚአብሔር በአፌ ያስቀመጠውን ብቻ ነው” ብሎ መለሰለት።
ባላቅም ከብቶችና በጎች ሠዋ፤ ከፊሉንም ለበለዓምና ከርሱ ጋራ ለነበሩት አለቆች ሰጣቸው።