ስለዚህ የሞዓብ አለቆች ወደ ባላቅ ተመልሰው፣ “በለዓም ዐብሮን ለመምጣት እንቢ አለን” አሉት።
በማግስቱም ጧት በለዓም ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፣ “ዐብሬአችሁ እንዳልሄድ እግዚአብሔር ከልክሎኛልና እናንተ ወደ አገራችሁ ተመለሱ አላቸው።”
ከዚያም ባላቅ ከፊተኞቹ ይልቅ ቍጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች አለቆች ላከ።
ባላቅ በለዓምን፣ “በቶሎ እንድትመጣ ልኬብህ አልነበረምን? ለምን አልመጣህም? በርግጥ ወሮታህን ልከፍል የማልችል ሆኜ ነውን?” አለው።