በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር መርዘኛ እባቦች ሰደደባቸው፤ ሕዝቡን ነደፉ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሞቱ።
እናንተ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፤ የመታችሁ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁ ደስ አይበላችሁ፤ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፤ ፍሬውም ተወርዋሪ መርዘኛ እባብ ይሆናል።
በኔጌብ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤ መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ ተባዕትና እንስት አንበሶች፣ መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣ መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣
“እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣ የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰድዳለሁ፤ እነርሱም ይነድፏችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።
“የዱር አራዊትንም በአገሪቱ ላይ ሰድጄ፣ አገሪቱን ሕፃናት አልባ ቢያደርጓትና ከአራዊቱም የተነሣ ምድሪቱ ሰው እስከማያልፍባት ባድማ ብትሆን፣
ከእነርሱ አንዳንዶቹ ጌታን እንደ ተፈታተኑና በእባብ ተነድፈው እንደ ጠፉ፣ እኛም ጌታን አንፈታተን።
በዚያ ጭልጥ ባለና አስፈሪ ምድረ በዳ፣ በዚያ በሚያስጠማና ውሃ በማይገኝበት ደረቅ መሬት፣ መርዘኛ እባብና ጊንጥ ባለበት ምድረ በዳ መራህ፤ ከጽኑ ዐለትም ውሃ አፈለቀልህ።