ስለዚህም እስራኤል በአሞራውያን ምድር ተቀመጠ።
የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያንን፣ የጌርጌሳውያንንና የኢያቡሳውያንን ምድር ነው።”
“እኛ ግን ገለበጥናቸው፤ ሐሴቦን እስከ ዲቦን ድረስ ተደመሰሰች፤ እስከ ኖፋ ድረስ ያሉትን፣ እስከ ሜድባ የተዘረጉትን እንዳሉ አፈራርሰናቸዋል።”
ሙሴ ሰላዮችን ወደ ኢያዜር ከላከ በኋላ እስራኤላውያን በአካባቢዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ እዚያ የነበሩትን አሞራውያን አባረሯቸው።
በፊታችሁ ተርብ ላክሁ፤ ይህም እነርሱንና ሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ጭምር ከፊታችሁ አሳደደ፤ ይህ ደግሞ በራሳችሁ ሰይፍና ቀስት ያደረጋችሁት አይደለም።