ከዚያም ተነሥተው እስከ አሞራውያን ግዛት በሚዘልቀው ምድረ በዳ ባለው በአርኖን አጠገብ ሰፈሩ፤ አርኖን በሞዓብና በአሞራውያን መካከል የሚገኝ የሞዓብ ወሰን ነው።
ከጐጇቸው ተባርረው ግራ እንደ ተጋቡ ወፎች፣ የሞዓብ ሴቶችም በአርኖን ወንዝ መሻገሪያ እንዲሁ ይሆናሉ።
ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤ የሞዓብን መደምሰስ፣ በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።
እንግዲህ በእግዚአብሔር የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በዚሁ የተነሣ ነው፤ “…በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብ አርኖንና
በለዓም በመምጣት ላይ መሆኑን ባላቅ በሰማ ጊዜ በግዛቱ ዳርቻ በአርኖን ወሰን ላይ ወደምትገኘው ወደ ሞዓብ ከተማ ሊቀበለው ወጣ።
ከዚያም እግዚአብሔር “አሁኑኑ ተነሡና የዘሬድን ደረቅ ወንዝ ተሻገሩ” አለን፤ እኛም ወንዙን ተሻገርን።
“የሞዓብ ዳርቻ ዔርን ዛሬውኑ ታልፋላችሁ።
“አሁኑኑ ተነሡና የአርኖንን ወንዝ ተሻገሩ፤ እነሆ፤ የሐሴቦንን ንጉሥ፣ አሞራዊውን ሴዎንንና አገሩን በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ፤ ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ጦርነት ግጠሙት።
“ቀጥሎም የኤዶምንና የሞዓብን ምድር በመዞር፣ በምድረ በዳው ተጕዞ ከሞዓብ በስተምሥራቅ በኩል በማለፍ ከአርኖን ማዶ ሰፈረ፤ የሞዓብም ድንበር አርኖን ስለ ነበር ወደ ሞዓብ ክልል አልገባም።