በሰሜን በኩል፤ የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣
ከዳን የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር፤
ከዳን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
በመጨረሻም የዳን ሰፈር ሰራዊት ለሁሉም ክፍሎች የኋላ ደጀን በመሆን በዐርማቸው ሥር ተጓዙ፤ አለቃቸውም የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር።
የሰራዊቱም ብዛት ስድሳ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ነው።
የሜራሪም ጐሣዎች ቤተ ሰቦች አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ይሆናል፤ የሜራሪም ጐሣዎች ከማደሪያው ድንኳን በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ።
በዐሥረኛው ቀን የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ስጦታውን አመጣ፤
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።