የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ ዘጠኝ ሺሕ ሦስት መቶ ነው።
ከስምዖን ነገድ የተቈጠሩት ዐምሳ ዘጠኝ ሺሕ ሦስት መቶ ነበሩ።
ከእነዚህ ቀጥሎ የስምዖን ነገድ ይሰፍራል፤ የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ሲሆን፣
ከዚያም የጋድ ነገድ ይቀጥላል፤ የጋድ ሕዝብ አለቃ የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ሲሆን፣
እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺሕ ሁለት መቶ ነበሩ።