በደቡብ በኩል፤ የሮቤል ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የሮቤል ሕዝብ አለቃ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ሲሆን፣
የእስራኤል የበኵር ልጅ የሮቤል ልጆች፤ ሮቤል የበኵር ልጅ ቢሆንም፣ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ፣ የብኵርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጥቷል። ከዚህም የተነሣ ትውልዱ የበኵርነቱን ተራ ይዞ ሊቈጠር አልቻለም።
“የሚረዷችሁም ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ “ከሮቤል የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤
ቀጥሎም የሮቤል ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር።
መለከቱ ከፍ ባለ ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲነፋ በስተ ደቡብ የሰፈሩት ነገዶች ጕዞ ይጀምሩ፤ ከፍ ያለው ድምፅ ጕዞ ለመጀመር ምልክት ይሆናል።
የሰራዊቱም ብዛት አርባ ስድስት ሺሕ ዐምስት መቶ ነው።
በአራተኛው ቀን የሮቤል ሕዝብ አለቃ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ስጦታውን አመጣ፤
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።