እናንተም ከእስራኤላውያን ላይ ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር መባ ታቀርባላችሁ፤ ከዚሁም የእግዚአብሔር ድርሻ የሆነውን ዐሥራት ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።
የልዑል አምላክ ካህን የነበረው የሳሌም ንጉሥ መልከ ጼዴቅም እንጀራና የወይን ጠጅ ይዞ ወጣ፤
ቍርባናችሁም ከዐውድማ እንደ ገባ እህል ወይም ከመጭመቂያ እንደ ወጣ ወይን ሆኖ ይቈጠርላችኋል።
ከምትቀበሉት ሁሉ ምርጥና እጅግ የተቀደሰውን ክፍል የእግዚአብሔር ድርሻ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ።’
ይህንም ግብር ከድርሻቸው ላይ ወስደህ የእግዚአብሔር ፈንታ በማድረግ ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው።
ይህም ስፍራ ኢየሱስ ስለ እኛ ቀድሞ የገባበት ነው። እርሱም እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኗል።