“የተቀደሱ ስለ ሆኑ የበሬ፣ የበግ ወይም የፍየል በኵር የሆኑትን አትዋጃቸውም፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ሥባቸውንም ሽታው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት አድርገህ ታቃጥለዋለህ።
አውራውንም በግ ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ርጨው።
ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።
እነዚህም አንድ ወር ሲሆናቸው ሃያ ጌራ በሚመዝነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ልክ፣ በተወሰነው በመዋጃው ዋጋ በዐምስት ሰቅል ጥሬ ብር ትዋጀዋለህ።