እርሱም፣ “ከእነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳን ራቁ የእነርሱ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትንኩ፤ አለዚያ በእነርሱ ኀጢአት ሁሉ እናንተም ትጠፋላችሁ” ሲል ማኅበሩን አስጠነቀቀ።
እንዳወጧቸውም፣ መልአኩ፣ “ሕይወታችሁን ለማትረፍ ፈጥናችሁ ሽሹ፤ መለስ ብላችሁ ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ከረባዳው ስፍራ እንኳ ቆም አትበሉ፤ ወደ ተራራው ሽሹ፤ አለዚያ ትጠፋላችሁ” አላቸው።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ! ተለዩ! ከመካከልዋ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ፤
“ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! ፈጥናችሁም ሕይወታችሁን አትርፉ! በኀጢአቷ ምክንያት አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነው፤ እርሱም የሥራዋን ይከፍላታል።
ሙሴ ተነሥቶ ወደ ዳታንና አቤሮን ሄደ፤ የእስራኤልም ሽማግሌዎች ተከተሉት።
ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።
ጳውሎስና በርናባስም ለማስጠንቀቂያ እንዲሆን የእግራቸውን ትቢያ አራግፈው ወደ ኢቆንዮን ሄዱ።
ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለመግዛት አስበሃልና፣ አንተም ገንዘብህም ዐብራችሁ ጥፉ!
“ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩም፤ ይላል ጌታ። ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ።”
እግዚአብሔር ከብርቱ ቍጣው ይመለስ ዘንድ ዕርም ነገሮች በእጅህ አይገኙ፤ እርሱ ምሕረቱን ያሳይሃል፤ ይራራልሃል፤ ለአባቶችህ በመሐላ ተስፋ በሰጠው መሠረት ቍጥርህን ያበዛዋል፤
በማንም ላይ እጅ ለመጫን አትቸኵል፤ ከሌሎችም ጋራ በኀጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽሕና ጠብቅ።
ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፤ ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፤ ከርሷ ውጡ፤