“ ‘ከአውራ በግ ጋራ በሂን ሢሶ ዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት ዐሥረኛ ልም ዱቄት የእህል ቍርባን አዘጋጁ፤
“ ‘መሥዋዕቱ ፍየል ከሆነ፣ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርብ፤
መሥዋዕቱን ይዞ የሚመጣው ሰው በሂን አንድ አራተኛ ዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ ዐሥረኛ የላመ ዱቄት የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ያቀርባል።
ለሚቃጠል ወይም ለዕርድ መሥዋዕት ከሚቀርብ ከእያንዳንዱ የበግ ጠቦት ጋራ የሂን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ የመጠጥ ቍርባን ዐብራችሁ አዘጋጁ።
እንዲሁም ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ አዘጋጁ፤ ይህንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ ያለው አድርጋችሁ አቅርቡ።