ልባችሁ የተመኘውን፣ ዐይናችሁ ያየውን ሁሉ ተከትላችሁ እንዳታመነዝሩ እነዚህን ዘርፎች በማየት የእግዚአብሔርን ትእዛዞች በማስታወስ እንድትታዘዙ ማስታወሻ ይሆኗችኋል።
ራሱ በመረጠው በስምንተኛው ወር፣ በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በቤቴል ባቆመው መሠዊያ ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ስለዚህ ለእስራኤላውያን በዓል ወሰነላቸው፤ ዕጣንም ለማቅረብ ወደ መሠዊያው ወጣ።
አረማመዴ ከመንገድ ወጣ ብሎ፣ ልቤ ዐይኔን ተከትሎ፣ ወይም እጄ ረክሶ ከሆነ፣
በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።
እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ።
የእግዚአብሔር ሕግ በከንፈራችሁ ላይ እንዲሆን ይህ በዓል ለእናንተ በእጃችሁ ላይ እንደ ታሰረ ምልክት፣ በእግራችሁ ላይ እንደሚገኝ መታሰቢያ ይሆንላችኋል። እግዚአብሔር በኀያል ክንዱ ከግብጽ አውጥቷችኋልና።
በራሱ የሚታመን ሞኝ ነው፤ በጥበብ የሚመላለስ ግን ክፉ አያገኘውም።
ልጄ ሆይ፤ ትምህርቴን አትርሳ፤ ትእዛዞቼን በልብህ ጠብቅ፤
አንተ ወጣት በወጣትነትህ ጊዜ ደስ ይበልህ፤ በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ፤ የልብህን መንገድ፣ ዐይንህ የሚያየውንም ሁሉ ተከተል፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ፣ አምላክ ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
በዚህ ፈንታ፣ በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ አባቶቻቸው ያስተማሯቸውን በኣሊምን ተከተሉ።”
እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
“እናታችሁን ምከሯት፤ ምከሯት፤ እርሷ ሚስቴ አይደለችም፤ እኔም ባሏ አይደለሁምና። ከፊቷ የዘማዊነት አስተያየትን፣ ከጡቶቿም መካከል ምንዝርናዋን ታስወግድ።
እንዲህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፣ በልቡ ራሱን በመባረክ፣ “እንደ ልቤ ሐሳብ ብኖርም እንኳ ሰላም አለኝ” ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።
አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባውን ኪዳን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር የከለከለውን ጣዖት በማንኛውም ዐይነት መልክ ለራሳችሁ አታብጁ።
ከባርነት ምድር ከግብጽ ያወጣህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ!
በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ።
ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብጽ ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን ትረሳለህ።
አመንዝሮች ሆይ፤ ከዓለም ጋራ ወዳጅነት ከእግዚአብሔር ጋራ ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኗል።