Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



ዘኍል 14:23

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለአባቶቻቸው እሰጣቸው ዘንድ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም። የናቀኝ ማንኛውም ሰው ፈጽሞ አያያትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንዶች ልጆቻቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛሃቸው፤ አባቶቻቸው ገብተው እንዲወርሱ ወዳዘዝሃቸውም ምድር አገባሃቸው።

በምድረ በዳ ሊጥላቸው፣ እጁን አንሥቶ ማለ፤

ስለዚህ እንዲህ ብዬ በቍጣዬ ማልሁ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም።”

በፊቴ ክፉ ነገር ቢያደርግና ባይታዘዘኝ፣ አደርግለታለሁ ብዬ ያሰብሁትን መልካም ነገር አስቀርበታለሁ።

ደግሞም ከምድር ሁሉ ይልቅ ውብ ወደሆነችው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ሰጠኋቸውም ምድር እንደማላስገባቸው እጆቼን አንሥቼ በምድረ በዳ በፊታቸው ማልሁ፤

ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤

ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።

‘በፍጹም ልባቸው ስላልተከተሉኝ ከግብጽ ከወጡት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች አንዳቸውም ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ በመሐላ ቃል የገባሁላቸውን ምድር አያዩዋትም፤

እነሆ፤ ይህችን ምድር ሰጥቻችኋለሁ፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ፣ ከእነርሱም በኋላ ለዘሮቻቸው ሊሰጥ የማለላቸውን ምድር ገብታችሁ ውረሱ።”

እኛ ያመንነው ግን ወደዚያ ዕረፍት እንገባለን፤ እግዚአብሔርም፣ “ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤ ‘ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም’ ” ብሏል። ይሁን እንጂ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የርሱ ሥራ ተከናውኗል።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች