እንግዲህ የእስራኤል ሰራዊት የጕዞ አሰላለፍ ሥርዐት ይህ ነበር።
እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣ እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?
እንዲሁም የንፍታሌም ነገድ ሰራዊት አለቃ የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር።
በዚህ ጊዜ ሙሴ የሚስቱን አባት የምድያማዊውን የራጉኤልን ልጅ ኦባብን፣ “እነሆ፤ እግዚአብሔር፣ ‘እሰጣችኋለሁ’ ወዳለን ምድር ጕዞ ጀምረናል፤ በመልካም ሁኔታ ስለምናኖርህ ከእኛ ጋራ ሂድ፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል በጎ ነገር ለማድረግ ቃል ገብቷልና አለው።”
ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ በየዐርማውም ሥር የሰፈሩትና፣ እያንዳንዳቸው በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የተጓዙት በዚህ ሁኔታ ነበር።
እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም። በቅዱሳን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሁ ነው።
ነገር ግን ሁሉም በአግባብና በሥርዐት ይሁን።
ምንም በሥጋ ከእናንተ ርቄ ብገኝ በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ነኝና በሥርዐት መኖራችሁንና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።