በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው።
ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ጠቅላላ ቍጥር ለንጉሡ አሳወቀ፤ በእስራኤል ስምንት መቶ ሺሕ፣ በይሁዳ ዐምስት መቶ ሺሕ ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ብቃት ያላቸው ሰዎች ተገኙ።
ከንፍታሌም ነገድ የተቈጠሩትም ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።
ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት በየቤተ ሰባቸው ተቈጠሩ፤
ሙሴና ካህኑ አሮን በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያንን በቈጠሩ ጊዜ ከእነዚህ ከተቈጠሩት መካከል አንዳቸውም አልነበሩም፤