ከንፍታሌም ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።
የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው።
“ንፍታሌም ነጻ እንደ ተለቀቀች፣ የሚያማምሩም ግልገሎች እንደምትወልድ ሚዳቋ ነው።
ከአሴር ነገድ የተቈጠሩት አርባ አንድ ሺሕ ዐምስት መቶ ነበሩ።
ከንፍታሌም ነገድ የተቈጠሩትም ዐምሳ ሦስት ሺሕ አራት መቶ ነበሩ።