የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር።
ካህኑ ኬልቅያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦርና፣ ሳፋን፣ ዓሳያም የሐርሐስ የልጅ ልጅ፣ የቲቁዋ ልጅ የአልባሳት ጠባቂውን የሴሌምን ሚስት ነቢዪቱን ሕልዳናን ለመጠየቅ ሄዱ። እርሷም ምክር በጠየቋት ቦታ፣ ኢየሩሳሌም ውስጥ በሁለተኛው የከተማው ክፍል ትኖር ነበር።
ሰባተኛው ወር በደረሰ ጊዜ፣ እስራኤላውያን በየከተሞቻቸው ሳሉ፣ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
“የቀሩት ሕዝብ፦ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ብለው ራሳቸውን ከጎረቤት አሕዛብ የለዩ ሁሉ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፣ የሚያውቁና የሚያስተውሉ ሁሉ ቃለ መሐላ ፈጸሙ፤
ከየቤተ ሰቡ አባቶችም አንዳንዶች ለሥራው የሚሆን 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,200 ምናን ብር ለግምጃ ቤቱ ሰጡ።
ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣