ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያድርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።
በሰንበት ዋዜማ በኢየሩሳሌም በሮች ላይ የምሽቱ ጥላ ማረፍ ሲጀምር በሮቹ እንዲዘጉና፣ ሰንበት እስኪያልፍ ድረስ እንዳይከፈቱ አዘዝሁ፤ በሰንበት ቀን ጭነት እንዳይገባም ከራሴ ሰዎች አንዳንዶቹን በየበሩ ላይ አቆምሁ።
ከእነርሱ ቀጥሎ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መልሰው ሠሩ፤ ከእነርሱም ቀጥሎ የሐናንያ ልጅ የመዕሤያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን መልሶ ሠራ።
በኢየሩሳሌምም ላይ ወንድሜን አናኒን እንዲሁም ፍጹም ታማኝና ከሌሎች ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔርን ይበልጥ የሚፈራውን የግንቡን አዛዥ ሐናንያን ኀላፊ አደረግኋቸው።
ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።
እርሱ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፤ ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳል።
“እንግዲህ፣ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብ የዋሃን ሁኑ።