ከዚህም በላይ በይሁዳ ምድር አገረ ገዥ ሆኜ ከተሾምሁበት፣ ከአርጤክስስ ሃያኛ ዓመት ጀምሮ እስከ ሠላሳ ሁለተኛው ዘመነ መንግሥቱ ድረስ፣ ለዐሥራ ሁለት ዓመት እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ ለአንድ አገረ ገዥ የተመደበውን ምግብ ተቀብለን አልበላንም።
የሐካልያ ልጅ የነህምያ ቃል፤ በሃያኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው ወር በሱሳ ግንብ ሳለሁ፣
ይህ ሁሉ ሲሆን እኔ በኢየሩሳሌም አልነበርሁም፤ ምክንያቱም በባቢሎን ንጉሥ በአርጤክስስ ሠላሳ ሁለተኛ ዓመት ተመልሼ ወደ ንጉሡ ሄጄ ነበር። ከጥቂት ጊዜም በኋላ የንጉሡን ፈቃድ ጠይቄ
በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር የወይን ጠጅ በመጣለት ጊዜ፣ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ በፊቱ ዐዝኜ አላውቅም ነበር፤
ዐምስት ታላንት የተቀበለው ሰው፣ ወዲያው በገንዘቡ ንግድ ጀምሮ ዐምስት ታላንት አተረፈ፤
ታዲያ ሽልማቴ ምንድን ነው? ሽልማቴማ ወንጌልን ስሰብክ በመብቴ ሳልጠቀም ወንጌልን ያለ ክፍያ መስበክ ነው።