በዚያ ጊዜ ለሕዝቡ፣ “ሌሊት ዘብ በመጠበቅና ቀን ሥራ በመሥራት እንዲያገለግለን እያንዳንዱ ሰው ከነረዳቱ በኢየሩሳሌም ይቈይ” አልኋቸው።
ስለዚህ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ሰዎች ጦራቸውን እንደ ያዙ ሥራውን ቀጠልን።
እኔም ሆንሁ ወንድሞቼ፣ ሰዎቼም ሆኑ ከእኔ ጋራ ያሉት ጠባቂዎች ልብሳችንን አላወለቅንም፤ ለውሃ እንኳ በምንሄድበት ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደ ያዘ ነበር።