እነዚህንም ሆሻያና ከይሁዳ አለቆች እኩሌቶቹ ተከተሏቸው፤
እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ።
የተከተሏቸውም ከዓዛርያስ፣ ከዕዝራ፣ ከሜሱላም፣