ተከታዮቹም ጌቤና ሳላይ 928 ወንዶች፤
በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ በተጻፈው መሠረት ከብንያም ነገድ የሕዝቡ ቍጥር ዘጠኝ መቶ ኀምሳ ስድስት ነበረ፤ እነዚህ ሁሉ ወንዶች የቤተ ሰብ አለቆች ነበሩ።
ከብንያም ዘሮች፦ የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ፣ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ፤
የእነዚህም አለቃ የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ሲሆን፣ የሐስኑአ ልጅ ይሁዳ የከተማዪቱ ሁለተኛ አውራጃ የበላይ ነበር።