በይሁዳ ከነበሩት ሌዋውያን ከፊሎቹ በብንያም ምድር ተቀመጡ።
እጅግ አስፈሪ የሆነ ቍጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፤ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።
በሎድና በኦኖ፣ ደግሞም ጌሃርሻም በተባለው ስፍራ ተቀመጡ።
ከሰላትያል ልጅ ከዘሩባቤልና ከኢያሱ ጋራ የተመለሱት ካህናትና ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣