ይህም በጠረጴዛው ላይ ለሚቀርበው ገጸ ኅብስት፣ ዘወትር ለሚቀርበው የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በሰንበት፣ በወር መባቻና በተደነገጉ በዓላት ለሚቀርበው መሥዋዕት፣ ለተቀደሱ መባዎች፣ ለእስራኤል ስርየት ለሚቀርበው የኀጢአት መሥዋዕትና ለአምላካችን ቤት ሥራ ሁሉ የሚውል ነው።
ሽታው ደስ የሚያሰኝ ዕጣን በፊቱ የሚታጠንበትን፣ የተቀደሰ እንጀራ በየጊዜው የሚቀርብበትን፣ በየጧቱና በየማታው፣ በየሰንበቱና በየመባቻው እንዲሁም በተወሰኑት በአምላካችን በእግዚአብሔር በዓላት የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበትን ቤተ መቅደስ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ሠርቼ እቀድስ ዘንድ አስቤአለሁ። ይህም ለእስራኤል የዘላለም ሥርዐት ነው።
የማስተስረያውን ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀብለህ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት አውለው፤ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ በማድረግ በእግዚአብሔር ፊት የእስራኤላውያን ማስተስረያ ይሆናል።”
እንግዲህ በምትበሉትም ሆነ በምትጠጡት ወይም በዓልን፣ ወር መባቻንና ሰንበትን በማክበር ነገር ማንም አይፍረድባችሁ፤
ካህን ሁሉ በየዕለቱ ቆሞ አገልግሎቱን ያከናውናል፤ ኀጢአትን ማስወገድ ከቶ የማይችሉትን እነዚያኑ መሥዋዕቶች ዘወትር ያቀርባል።