ወንድሞቻቸው፦ ሰበንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን፣
የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤ የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።
ከሌዋውያኑም መካከል፤ ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።
በአራተኛው ቀን ብሩን፣ ወርቁንና ንዋያተ ቅድሳቱን በአምላካችን ቤት መዝነን ለኦርዮ ልጅ ለካህኑ ለሜሪሞት በእጁ አስረከብነው፤ ከርሱም ጋራ የፊንሐስ ልጅ አልዓዛር፣ ሌዋውያኑ የኢያሱ ልጅ ዮዛባትና የቢንዊ ልጅ ኖዓድያ ነበሩ።
ሚካ፣ ረአብ፣ ሐሸብያ፣
ሌዋውያኑ፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ከኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣
ሌዋውያኑ ደግሞ ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እንዲሁም ከወንድሞቹ ጋራ የምስጋና መዝሙር ኀላፊ የሆነው መታንያ ነበሩ።
ከርሱም ቀጥሎ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማእዘኑና እስከ ማእዘኑም ጫፍ ያለውን ሌላውን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሠራ፤
ሌዋውያኑ፦ በሆዳይዋ በኩል የኢያሱና የቀድምኤል ዘሮች 74
ሌዋውያኑ ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን፣ ፌልያ ሕዝቡ በዚያው ቆመው እንዳሉ ሕጉን አስረዷቸው።