ጠባቂዎችሽ እንደ አንበጣ፣ መኳንንትሽም በብርድ ቀን በቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ ኵብኵባ ናቸው፤ ፀሓይ ሲወጣ ግን ይበርራሉ፤ ወዴት እንደሚበርሩም አይታወቅም።
“በምድር ሁሉ ላይ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ! በሕዝቦች መካከል መለከትን ንፉ! ሕዝቦችን ለጦርነት በርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትን፣ የሚኒንና የአስከናዝን መንግሥታት፣ ጠርታችሁ በርሷ ሰብስቧቸው፤ የጦር አዝማች ሹሙባት፤ ፈረሶችንም እንደ አንበጣ መንጋ ስደዱባት።
ከአሕዛብ ወገን እጅግ ጨካኝ የሆኑትም ባዕዳን ሰዎች ቈራርጠው ጣሉት። ቀንበጦቹ በተራራዎቹና በሸለቆዎቹ ሁሉ ላይ ወድቀዋል፤ ቅርንጫፎቹም በውሃ መውረጃዎቹ ሁሉ ላይ ተሰባብረው ወድቀዋል፤ የምድሪቱ ሰዎች ሁሉ ከጥላው ሥር በመውጣት ትተዉት ሄደዋል።
ብሩን ዝረፉ! ወርቁን ንጠቁ! በየግምጃ ቤቱ ያለው፣ የተከማቸውም ሀብት ስፍር ቍጥር የለውም።
አንበጦቹ ለጦርነት የተዘጋጁ ፈረሶች ይመስሉ ነበር፤ በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ደፍተዋል፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር፤